Notice of Nondiscrimination: Amharic

መብቶችዎን ይወቁ

 በጤና እና በሰብአዊ አገልግሎት የቋንቋ ተደራሽነት

የ Sawtooth Mountain Clinic የአሜሪካ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ) በአሜሪካ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የሚያስፈልገውን የጤና እንክብካቤ እና ሰብአዊ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችል ማረጋገጥ ይፈልጋል። ይህ እንግሊዝኛ ቋንቋን በደንብ የማይናገሩ ሰዎችን እና አካል ጉዳተኞችን ያካትታል። HHS ሁሉም ሰው በፍትሃዊነት እና በአክብሮት መስተናገድ እንዳለበት ያምናል።

የ Sawtooth Mountain Clinic የሲቪል መብቶች ቢሮ) በእርስዎ ዘር፣ ቀለም፣ በሃገርዎ፣ ጾታ፣ ዕድሜ፣ ሀይማኖት እና አካል ጉዳት ላይ በመመርኮዝ በጤና እና በሰብአዊ አገልግሎቶች ላይ ከሚደርስ መድልዎ የሚከላከሉ ህጎችን ያስፈጽማል። HHS OCR የህክምና መዝገቦችዎን ግላዊነት እና ደህንነት የሚጠብቁ ህጎችንም ያስፈጽማል።

በአብዛኛዎቹ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞች በዘርዎ፣ በቀለምዎ፣ በሃገርዎ፣ በጾታዎ፣ በእድሜዎ፣ በሀይማኖትዎ ወይም ባለብዎት አካለ ጉዳት ምክንያት የጤና እንክብካቤ ሽፋን ወይም ህክምና ሊከለከሉ አይችሉም።

የቋንቋ እገዛ ለሁሉም ሰውአስፈላጊ መብቶች

  • እንደ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች ወይም ማህበራዊ አገልግሎቶች ባሉ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች አገልግሎት ከማግኘት ሊታገዱ ጥቅማጥቅሞችዎን ሊከለከሉ ወይም መድልዎ ሊደርስብዎት አይችልም።
  • በአካልም ሆነ፣ በ ቴሌ ጤና፣ በ ድህረ-ገጾች እና የሞባይል አፕሊኬሽኖችን ጨምሮ በርቀት ከአድልዎ ፀዱ የሆነ የጤና እንክብካቤን የማግኘት መብት አልዎት።
  • የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎችዎ እንክብካቤያቸዎን ወይም አገልግሎቶቻቸውን በሚፈልጉበት ጊዜ እርስዎ ሊረዱት በሚችሉበት መንገድ ከእርስዎ ጋር መነጋገር እንደሚችሉ ማረጋገጥ አለባቸው።
  • እርስዎ ወይም ከእርስዎ ጋር ያለ ሰው እንግሊዘኛ በደንብ የማይናገሩ ከሆነ ወይም እንግሊዘኛ ማንበብ፣ መጻፍ፣ መናገር ወይም መረዳት ካልቻሉ፣ በቋንቋ አገልግሎቶች (እንደ አስተርጓሚ ወይም ትርጉም) ያሉ አገልግሎቶችን ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ በነጻ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።
  • የእራስዎን አስተርጓሚ ይዘው መምጣት፣ ለአስተርጓሚ መክፈል፣ ወይም ልጅ ወይም የቤተሰብ አባል እንዲተረጉሙልዎ መተማመን አይጠበቅብዎትም።
  • አካል ጉዳተኛ ከሆኑ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ መረጃን ለማግኘት የሚረዱ፣ አጋዥ እርዳታዎች እና አገልግሎቶች የሚባሉ መሳሪያዎችን እና አገልግሎቶችን ከክፍያ ነጻ ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ የት ማግኘት ይችላሉ?

በቋንቋ ተደራሽነት ላይ እርዳታ ለማግኘት የሚከተለውን ኢሜይል frontdesk@sawtoothmountainclinic.org

በሲቪል መብቶች እና የጤና መረጃ ግላዊነት ላይ እርዳታ ለማግኘት የሚከተለውን ይጎብኙ፡-www.hhs.gov/ocr

እንዴት ነው ቅሬታ የሚያቀርቡት?

እርስዎ ወይም ሌላ ሰው በዘር፣ በቀለም፣ በመጡበት አካባቢ፣ በጾታ፣ በእድሜ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ፍትሃዊ ያልሆነ አያያዝ ወይም መድልዎ ደርሶብናል ብለው ካሰቡ ወይም የእርስዎ ወይም የሌላ ሰው የጤና መረጃ ሚስጥራዊ አልተደረገም ብለው ካሰቡ ለHHS OCR መንገር ይችላሉ።

  • እንደ የቤተሰብ አባል፣ የጥብቅና ድርጅት፣ ጓደኛ ወይም የስራ ባልደረባ ያለ አንድ ሰው እርስዎን ወክሎ ቅሬታ ሊያቀርብልዎ ይችላል።
  • HHS OCR መረጃን በተለያዩ ቅርፀቶች (እንደ ብሬይል ወይም ትልቅ ህትመት) ሊያቀርብ ይችላል እና እርስዎን ለመርዳት እንደ ማስተላለፊያ አገልግሎት ወይም የቋንቋ እገዛ ያሉ ነጻ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ቅሬታ ማቅረብ ወይም HHS OCR ማነጋገር፦

ድህረ ገጽ | ኢሜይል፦ OCRMail@hhs.gov | ስልክ፦ 1-800-368-1019 | TDD 1-800-537-7697

አማርኛ